ሀገሬ ቲቪ

ተደጋጋሚ ግጭቶች የሚከሰቱበት የኮንሶ ዞን

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኮንሶ ዞን እና በደራሼ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ሆልቴ (ኮማይቴ ማዞሪያ) አካባቢ በተደጋጋሚ በሚነሱ ግጭቶች የዜጎች ህይወት እየተቀጠፈ ነው አለ።ፓርቲው ጉዳዩን አስመለከቶ መግልጫ አውጥቷል።በመግለጫው ላይ እንዳመለከተውም በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን እና በደራሼ ልዩ ወረዳ ለዓመታት ባልተፈታ ቅሬታና ተደጋግሞ በሚነሳ የመዋቅር ጥያቄ ምክንያት ንጹኃን ዜጎች በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ቅንጦት ከሆነባቸው ቆይቷል ብሏል ፓርቲው።ከሰሞኑ በተፈጠረው የታጡቁ ኃይሎች ጎብኚዎችን የማገት እና እነሱን ለማስለቀቅ የተሰማሩ የፀጥታ አካላትን ማጥቃት አካባቢው ከወትሮው በተለየ የደህንነት ስጋት ውስጥ እንደገባ አመላካች ነው ብሏል ፓርቲው። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ንጹኃን ዜጎች እና የአካባቢው የጸጥታ አካላት በዚሁ ምክንያት ሕይወታቸው መቀጠፉን ኤዜማ አስታውቋል፡፡በዚህ ግጭት እጃቸው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያለበት፣ ከፊትም ሆነ ከጀርባ ሆነው ጉዳዩን የሚዘውሩ እና የተሳተፉ ኃይሎች ተለይተው አጥፊዎቹ ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መልኩ በአፋጣኝ ወደ ህግ እንዲቀርቡ እና ተገቢውም ቅጣት እንዲያገኙ ፓርቲው አሳስቧል

በሀገሬ ቲቪ
2022-04-28