ሀገሬ ቲቪ

የቋሚ ንብረት ሥም ዝውውር አገልግሎት ታገደ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ሥም ዝውውር አገልግሎት፤ ከትናንት ኀዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ በጊዜያዊነት መታገዱ ተገለጸ።

አገልግሎቱ የታገደው በከተማዋ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሒደት ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት፤ የካቢኔ ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ ቢኒያም ምክሩ መግለጻቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ለሚመለከታቸው አካላትም የተላለፋው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ መሰጠቱንም ሃላፊ ጨምረው ገልጸዋል።

በብሩክ ያሬድ
2022-12-09