ሀገሬ ቲቪ

የወባ በሽታ ስርጭት ጨመረ

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ወቅት በነበረው መዘናጋት የወባ በሽታ ስርጭት እንደጨመረ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ63 ሺ በላይ ሰዋች ለሞት ሲዳረጉ፤ ከ13 ሚለዮን በላይ ሰወች በወባ በሽታ መያዛቸውን ድርጅቱ በሪፖርቱ አመላክቷል። በበሽታው ከተያዙት ውስጥም 95 በመቶዎቹ አፍሪካ ውስጥ ናቸው ተብሏል ።

ድርጅቱ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እየታገለ ቢገኝም ፀረ-ተባይ መድሀኒቶችን የሚላመድ አዲስ የወባ ዝርያ መገኘቱ እና የገንዘብ ድጋፍ ማጣቱ መሰናክል እንደሆነበት ገልጿል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-12-09