
በየሁለት ዓመቱ የሚደረገው የጀርመን አፍሪካ የንግድ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ተጀመረ።
የጀርመን ኩባንያዎች በአፍሪካ ባለፈው ዓመት ከ1.6 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
ጉባኤው በጀርመን እና አፍሪካ መካከል ያለውን የንግድ አጋርነት እንደሚያሳድግ በጉባኤው ላይ የተገኙት የጀርመን የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ሮበርት ሀቤክ ገልፀዋል።
የጀርመን መንግስት የሀገሪቱ ኩባንያዎች በአፍሪካ ላይ መዕዋለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ማበረታቻዎችን እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በዮሴፍ ከበደ
2022-12-09