አሜሪካ እና ሩሲያ የእስረኛ ልውውጥ አደረጉ። ሩሲያ በአደንዣዥ ዕፅ ዝውውር ከሳ በእስር ላይ ያቆየቻትን የአሜሪካ ዝነኛዋ የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ብሪትኒ ግሪነርን ለአሜሪካ ስትሰጥ።
በአሜሪካ በበኩሏ በህገወጥ ዓለም አቀፍ የመሳሪያ ንግድ ፈርዳበት ዘብጥያ አውርዳው የነበረውን ቪክቶር ቦወት ለሩሲያ መልሳለች።
በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት የተደረገው የእስረኛ ልውውጥ ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከፍተኛ ስኬት ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
የአሜሪካ ድርድር ላለፉት 2 ዓመታት በሩሲያ እስር ቤት የሚገኘውን የሚቺጋን ኮርፖሬት የደህንነት ኃላፊ ዌላንን ማስለቀቅ አለመቻሏ፤ የባይደን አስተዳደር በሩሲያ ጫና ውስጥ መሆኑን አመላካች ነው እየተባለም ይገኛል።
በማህሌት አማረ
2022-12-09
