የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጅ ዞን መልካ ጉባ ባደረገው ዘመቻ አካባቢውን ከሸኔ ታጣቂ ቡድን ነፃ ማድረጉን አሳወቀ።በዚህ ዘመቻ በአካባቢው ለ4 ዓመታት ያህል በህዝቡ ላይ ስቃይ ሲያደርሱ ከነበሩ የቡድን ታጣቂዎች መካከል በርካታዎች መደምሰሳቸው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል። የዕዙ የኋላ ደጀን አስተባባሪና የኦፕሬሽኑ መሪ ኮሎኔል ግርማ አየለ በዚህ ውጊያ ከ200 በላይ የሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን፣ ከ100 በላይ መቁሰላቸውንና 22 መማረካቸውን ተነግረዋል። ሽብርተኛነት የተፈረጀው ሽኔ በቦታው በርካታ ዜጎችን በመግደል በጅምላ መቅበሩን ኮሎኔል ግርማ አየለ ተናግረዋል። መልካ ጉባ በተፈጥሮው በአስቸጋሪ የመሬት ገፅና ከፍተኛ የውሃ ሙላት ባለው ዳዋ ወንዝ መከበቡ፣ ሸኔን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች በአካባቢው መገኘታቸው፣ ታጣቂ ቡድኑ ለአመታት በአካባቢው በመንቀሳቀስ ይዞታውን ማስፋቱ በዘማቻው የነበሩ ፈታኝ ሁኔታዎች ነበሩ
በሀገሬ ቲቪ
2022-04-28
