ሀገሬ ቲቪ

በሉከርቢ ቦንብን የሰራው ግለሰብ በዩኤስ እስር ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

በሉከርቢ የአሜሪካ ንብረት የነበረውን የፓን ኤ ኤም አውሮፕላንን ያወደመውን ቦምብ የሠራ አንድ ሊቢያዊ ሰው በዩናይትድ ስቴትስ እስር ቤት እንዳለ የስኮትላንድ ባለ ሥልጣናት ተናግረዋል።

በአሜሪካ ለሁለት ዓመት በእስር ላይ የሚገኘው አቡ አጊላ ማሱድ ከ34 አመት በፊት በሉከርቢ በተከሰከሰው አውሮፕላን የቦንብ ፍንዳታ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርጓል በሚል ነው አሜሪካ ለእስር የዳረገችው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

በፓን ኤኤም ቦይንግ 747 አውሮፕላን ተሳፋሪዎችን እና የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 270 ሰዎች በእንግሊዝ ምድር ህይወታቸውን አጥተዋል።

በማህሌት አማረ
2022-12-12