አውሮፓዊቷ ሀገር ስሎቫንያ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ጊዜያዊ አባል ለመሆን የአንጎላን እገዛ ጠየቀች።
የስሎቫኒያ ምክትል ጠ/ሚኒስትር በአንጎላ ሲካሄድ በነበረው አስረኛው የአፍሪካ ካሪቢያን እና ፓስፊክ ሃገራት ጉባኤ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው ሀገሪቱ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የጊዜያዊ አባልነት መቀመጫ ለማግኘት የአንጎላን ድጋፍ እንደምትሻ የተናገሩት።
የስሎቫኒያ ምክትል ጠ/ ሚኒስተር ታንጃ ፋጆን በሉዋንዳ በተካሄደው ጉባኤ ላይ በተገኙበት ወቅት ሃገራቸው ስሎቫኒያ ከአፍሪክ ጋር በዲፕሎማሲው መስክ አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።
ስሎቫንያ ለጸጥታው ምክር ቤት አባልነቷ የአፍሪካ እና ካሪቢያን ሀገራትን ድጋፍ ትፈልጋለች ሲል የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው።
በማህሌት አማረ
2022-12-12
