ሀገሬ ቲቪ

ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ የሚታመን የ27 ስደተኞች አስክሬን በዛምቢያ ተገኘ

በዛምብያ ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ የሚታመን የ27 ስደተኞች አስክሬን ተጥሎ ተገኘ። የዛንቢያ ፖሊስ አስክሬኖቹን ከከተማ ወጣ ባለ አንድ የእርሻ ቦታ ላይ ማግኘቱን የሀገሪቱ ሹማምንት አስታውቀዋል።

ዕድሜአቸው ከ20 እስከ 38 የሚገመት ሁሉም ወንዶች የኾኑ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች መኾናቸው ተገልጿል። የሞታቸው ምክንያት ርሀብ እና ድካም መቋቋም አቅቷቸው ሊኾን እንደሚችል ተገምቷል።

በሕይወት የተረፈ አንድ ሰው መገኘቱን እና ለሕክምና ‘’ሉሳካ’’ ወደተሰኘ ሆስፒታል እንደተላከ ሮይተርስ ዘግቧል። ቀሪዎቹ አስክሬኖች ወደ ሬሳ ምርመራ ክፍል ተወስደዋል።

አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ዛምቢያን እንደመሻጋሪያ ይጠቅሟታል ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-12