ሀገሬ ቲቪ

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ በሞት የተለዩበት ቀን

በኢትዮጲያ የዘመናዊ ታሪክ ወስጥ ሰማቸው በጉልህ ይጠቀሳል ። በኢትዮጲያም ብሎም በአፍሪካ ታላቅ ድልን የተቀዳጁ መሪም ናቸው ። ዳግማዊ አጼ ምኒሊክ ።

ንጉሰ ነገስቱ ለኢትዮጲያ የዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት አስተዋውቀዋል ።ታዲያ እኚሁ ንጉስ መሞታቸው ለህዝብ የተረዳው በዛሬው ቀን ከ109 አመት በፊት ነበር ። የአለቱን ከታሪክ ትኩረታችን ነው ። ወንድምአገኝ አበበ ።

በኢትዮጲያ ዘመን አይሽሬ ንጉስ ናቸው። አለም በአድዋ ጦርነት አይረሳቸውም ። ለዘመናዊ ኢትዮጲያ መፈጠር ምክንያትም ተደርገው ይጠራሉ ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ አጼ ምንሊክ።

ዳግማዊ አጼ ምንሊክ በኢትዮጲያ ጥቅምት 25 ቀን 1882 ዓ.ም ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው ከነገሱ በኋላ ለሃገራቸው ብዙ ታላላቅ ሰራዎችን ሰርተዋል ፡፡

ንጉሰ ነገስቱ በነገሱ ማግስት የመጀምሪያው ተግባራቸው ይህ ነበር ።እንግዲህ ንጉስህ እኔ ነኝ እና የሸፈትህ እና የኮረፈክ ሁሉ ምሬሃለው ና ለኢትዮጲያ ግባ ሲሉ የሰላም ጥሪን አስተላለፉ። ይህ የሰላም ጥሪ በመከፋፈል ወስጥ የነበረውን የኢትዮጲያ ህዝብ ወደ አንድነት እንደሳበም ይነገራል ።

ንጉስ ነገስቱ ከነገሱ ከ6 አመት በኋላ ኢትዮጲያ እና የአትዮጲያን ህዝብ በባርነት ለመጣል የመጣውን ወራሪ የጣሊያን ጦር በሽንፈት መልሰዋል ። ንጉሱ በአድዋ ጦርነት መጀመሪያ ላይ ዘር ፣ ጎሳን ሳይለያይ ለኢትዮጲያውያን ያስተላለፉት የክተተ አዋጅ ዛሬም ድረስ ይታወሳል ።

ዳግማዊ አጼ ምንሊክ በንግስና ዘመናቸው የአድዋ ጦርነት ጣሊያን ድል ከማድረጋቸው ባሻገር ለዘመናዊ ኢትዮጲያ መፈጠር ምክንያት ሆንዋል። ለቴክኖሎጂ መጎልበት ከነበራቸው ቀናኢነት የተነሳ ሙሉ አፍሪካ በባርነት ሲማቅቅ እሳቸው ግን ሃገራቸው ኢትዮጲያ አውሮፓዊያን ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ቲክኖሎጂዎችን በኢትዮጲያ አስጀመረው ነበር ።

ለአብነትም ሰልክ ፣ የፖስታ አገግልግሎት ፣ የኤሌትሪክ ሃይል እንዲሁም ዘመናዊ ትምህርትን ጨምሮ ከሃያ በላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በኢትዮጲያ አስጀምረዋል ።ይህን ያደረጉት ንጉስ የሰልጣን ማብቂያቸው መጀመሪያ ተደርጎ የሚሰ ወደው ቀን ነሐሴ 3 ቀን 1900 ዓ.ም ነው።

ንጉስ ቤተክርስቲያን ደርሰው ሲመለሱ ከእልፍኛቸው አጠገብ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው በድንገት ወደ መሬት ዝቅ ብለው ሸብረክ አሉ፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችም በቶሎ አንስተው ወደ ውስጥ አስገቧቸው።

ከዚህያን ግዜ አንስቶ ንጉስ ምኒልክ ሕመማቸው እየበረታ ሄደ ፡፡በህመም አልጋ ላይ የወደቁት ንጉስ ነገስቱ የጤናቸው እንዲሻሻል በጸበል እና በአውሮፓዊያን የህክምና ባለሞያዎች ሲረዱ ቢቆዩም ሊተርፉ አልቻሉም ።

ምንም እንኳ የአጤ ምኒልክ መሞት ወሬው እንዲደበቅ ቢደርግም የከተማው ህዝብ ሰምቶት ነበርና "እምዬ ጌታዬ" እያለ በየቤቱ በድብቅ እያለቅሰ ነበር።

በዘመናቸው ሁሉ ክፋትን በይቅርታ ጥፋትን በትዕግስት እያለፉ፤ ሀገር የምትሰፋበትና የምትለማበትን፤ ሕዝብ ሰላምና ስልጣኔ የሚያገኝበትን መንገድ ሲያስቡና ሲፈፅሙ የነበሩት ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ከዓመታት በፊት የጀመራቸው በሽታ ፀንቶባቸው በዕለተ አርብ ታህሳስ 3 ቀን 1906 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞተ መለየታቸው ተረዳ ።

ጸሃፍት እንድሚሉት የንጉስ ሞት ከህዝባቸው ለ ሁለት አመት በደብቅ ተይዞ ነበር ። ህዝብም በንጉስ ሞት ታላቅ ሃዘን ውስጥ ወደቀ ።በመቀጠልም ለንጉሳቸው እንዲህ ሲል ገጠሙ ።

"ፈረስ በቅሎ ስጠኝ ብዬ አለምንህም
አምና ነበር እንጂ ዘንድሮስ የለህም"

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-12