ሀገሬ ቲቪ

የበጎ ፈቃደኞች በሰሜኑ ጦርነት

በኢትዮጵያ በሚከሰቱ አደጋዎች ወቅት ፈጥኖ ምላሽ በመስጠት ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር።

ማኅበሩ ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀንን ዛሬ አክብሯል። በጎ ፈቃደኞች ለማሕበሩ የጀርባ አጥንት መሆናቸው በመድረኩ ተነስቷል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ወቅትም እኚሁ የበጎ ፈቃደኞች የማይተካ ሚና መጫወታቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ፀሐፊ አቶ ጌታቸው ጣአ ነግረውናል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ200 ሺሕ በላይ በጎ ፈቃደኞችን የያዘው መኅበሩ፤ በጦርነቱ ግዜ በነበረው የበጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ ቀላል የማይባል ሀብት ማትረፉን ሰምተናል።

ማሕበሩ በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ምላሽ ለመስጠት በዓመት እስከ 40 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አባላት እና በጎፈቃደኞች መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ዳዳ ነግረውናል።

ማኅበሩ በጎ ፈቃደኞችን በስፋት ለማሳተፍ በጎ ፈቃደኞችን ካሉበት በኦን ላይን የመመዝገብ ስራ መጀመሩን ሰምተናል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-12-12