የቤልጂየም ፖሊስ የአውሮፓ ፓርላማ ምክትል ፕሬዝዳንቷን ጨምሮ 4 ሰዎች ላይ ክስ መስርቷል ።
የቤልጂየም ፖሊስ ከሙሰና ጋር ተያያዞ የህብረቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ኢቫ ካይሊን ጨምሮ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
አባላቱ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኳታር የፓርላማውን ድጋፍ ለማግኘት ለባለስልጣናት ሰጥታለች በተባለው ጉቦ ምክንያት ተብሏል።ይህን ወንጀል ተከተሎ ምርመራ እያደረገ የሚገኘው የቤልጂየም ፖሊስ በመዲናው የሚገኘውን የህብረቱ የፓርላማ ቢሮዎች ላይ ፍተሻ አካሂዶባቸዋል።
ፍተሻዎቹ የተጀመሩት አርብ ዕለት ሲሆን እስከ አሁን ለ 20 ግዜያት ፍተሻ ማካሄዱን አስታውቋል ።ይህን ክስተት ተከተሎ የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ሮቤታ ሜትሶላ “ዴሞክራሲ አደጋ ላይ ነው” ሲሉ የፓርላማ አባላቱን አስጠንቀቀዋል።
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ፎን ደር በበኩላቸው ክሶቹ "እጅግ ከባድ" በመሆናቸው ተጨማሪ መርማሪ አካል እንዲቋቋም ጠይቀዋል።
ኳታር በኩሏ እንዲህ አይነቱን ተግባር አለፈጸምኩም ስትል አስታውቃለች።ኳታር ለህብረቱ ባለስልጣናት ሰጥታዋለች የተባለውን ገንዘብ በፓርላማው ታሪክ ውስጥ ከተከሰቱት የሙስና ተግባራት በታሪክ ትልቁ ነው ተብሏል ። የህብረቱ የፓርላማ አባላት ከዚህ ሙስና ጋር በተያያዘ ለስብሰባ ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
የቤልጂየም አቃቢ ህግ እንዳስታወቁት ወደ 600 ሺህ ዩሮ የሚገመት ገንዘብ በአንድ ተጠርጣሪ ቤት፣ 150 ሺህ ዩሮ በሌላኛው የህብረቱ ፓርላማ አባል መኖሪያ እና በበዙ መቶ ሺዎች የሚገመት ዩሮ በሻንጣ ውሰጥ በብራስልስ ሆቴል ውስጥ ተገኝቷል ብለዋል።
ይህን ተከትሎ የተጠርጣሪዎቹ ፓርላማ አባላት ኮምፒውተሮች እና ተንቀሳቃሽ ስልኮች ለተጨማሪ ምርመራ ወስዷቸዋል ።
ፖሊሶቹ ከዓርብ ጀምሮ ለምርመራው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እንዳይጠፉ ለመከላከል ሲሉ 10 የሚደርሱ የፓርላማ አባላት የትኛውንም የኢሜይልና ሌሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መረጃዎቻቸውን እንዳይለዋወጡም ታግደዋል።
የቤልጂየም አቃቢ ህግ በተያዙት ተጠረጣሪዎች ላይ ከወንጀለኛ ተቋም ጋር በመሰራት ፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና በሙሰና ወንጀል በመሳተፍ በሚል ክስ መመሠረቱን አስታወቋል ።
የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዘዳንት ሜሶላ በበኩላቸው ለስምንት ዓመታት የህብረቱ የፓርላማ አባል እና ምክትል ፕሪዛዳንት የነበርችውን ኢቫ ካይሊ ከስራዋ አግድዋታል ። በግሪክ የሚገኙ አቃቢ ህጎችም የኢቫ ካይሊ ንብረቶች እንዳይነቀሳቀሱ ማገዳቸው ተሰማቷል።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-13
