ሀገሬ ቲቪ

ለሁለት ቀናት ያለማቋረጥ ኳስ ያንጠባጠበው ብራዚላዊ

የአለም ዋንጫ እያዘጋጀች ያለችው ኳታር ከእግር ኳሱ ጎን አጓጊ እና አስገራሚ ክስተቶችን በማስተናገድ አለም ከእግር ኳሱ ባለፈምም በአይረሴ ክስተቶቹ እንዲዝናና እያደረገች ትገኛለች፡፡

ታዲያ ይህችው በየቀኑ አዳዲስ ክስተቶችን እያስተናገደች ያለችው ኳታር ከብራዚል በመጣ አንድ ታዳሚ ደምቃለች፡፡ ይህ ብራዚላዊ ወደ ኳታር ሲያቀና የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ለመታደም ብቻ ሳይሆን የራሱንም የአለም ሪከርድ ለማሻሻል አቅዶ ነው የተጓዘው።

ሪካርዶ የተሰኘው ይሄው ግለሰብ ወደ ኳታር ሲያቀና ለ48 ሰአታት ወይንም ለሁለት ቀናት ያህል ኳስ መሬት ሳያሳርፍ ለማንጠባጠብ እቅድ ይዟል። በ2021 ለ 34 ሰአት ከአምስት ደቂቃ ኳስን በማንጠባጠብ የአለምን ሪከርድ ይዟል።

ሪካርዶ በ2021 ይዞት የነበረውን ኳስን ሳያሳርፉ ማንጠባጠብ የአለም ሪከርድ የፊፋን የአለም ዋንጫ እያስተናገደች ባላቸው ኳታር ለ48 ሰአታት በማንጠባጠብ የራሴን ሪከርድ አሻሽላሉ ማለቱ ተሰምቷል። ኳሱንም ከዛሬ ጀምሮ ማንጠባጠብ ጀምሯል።

ታዲያ ይሄ ሰውየ ሳይበላ ሳይጠጣ የተፈጥሮ ህግ አለ መፀዳዳት የሚባል ነገር ታዲያ እንዴት ነው ለሁለት ቀናት ያክል አቅም ኑሮት ያለማቋረጥ ኳስን ያህል ነገር እንዴት ያንጠባጥባል የብዙዎች ጠያቄ ነው። ሪካርዶ ደግሞ ይሄ ለኔ ከዕለት ተለት እንቅስቃሴየ ለይቼ አላየውም ቀላል ነው ይላል።

እንደ ሁል ጊዜው መፀዳጃ ቤት ስሄድ፣ ምግቤን ስበላ፣ ጥርሴን ስቦርሽም በተመሳሳይ ሰዓት ኳስ ማንጠባጠብ እችላልሁ አንድ የማልችለው ነገር ቢኖር መተኛት ብቻ ነው ብሏል።

ይሄንን ለማድረግ በመንፈስም ሆነ በአካል ጠንካራ መሆንን ይጠይቃል ያለው ሪካርዶ ያለምንም እረፍት መስራት ጤናን ጨምሮ ብዙ ነገሮችን ይጎዳል ብሏል።

ሪካርዶ ኳስ ማጠባጠቡን ዛሬ ጀምሮታል። በ2021 ኳስ ያለማቋረጥ ባንጠባጠበበት ጊዜ በመጨረሻ ሰአት እራሱን ስቶ የወደቀው ሪካርዶ ባሁኑ እንዳሰበው 48 ሰአቱን ሙሉ አንጠባጥቦ ይጨርስ ይሆን ወይንስ የሚለውን አብረን የምንሰማ ይሆናል።

በማህሌት አማረ
2022-12-13