ሀገሬ ቲቪ

የሥራ አጥ ቁጥር መጨመር መንስዔ

በአጫጭር ስልጠናዎች እና በሙያ እና ቴክኒክ የሰለጠኑ ቶሎ ሰራ የመቀጠር እድላቸው ሰፊ እንደሆነም የት/ርት ሚኒስቴር ዲኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልፀዋል። የጉልበት ገበያ ስርዐታችንን ማዘመን ለችግሩ መፍትሄ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

በየአመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከየከፍተኛ የት/ርት ተቋማቱ ይመረቃሉ። ነገር ግን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቆ የሚዎጣው የስራ አጥ ቁጥር የትየለሌ ነው።

በቅርቡ በግል የክፍተኛ ት/ርት ተቋማት ሳይጨምር በመንግስት ዩንቨርስቲዎች የተመረቁት 58 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ስራ እንድሚያገኙ በት/ሚኒስተር መገለፁ ይታወሳል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የት/ሚኒስተር ዲኤታ ያለው የተማረ የሰው ሃይል ኢኮኖሚው ከፈጠረው የሰራ እድል ጋር አለመጣጣሙ አንዱ ችግር ነው ብለዋል።

ሃገሪቱ ካላት ኢኮኖሚ እና ኢንደስትሪዎች ካላቸው አቅም አንፃር በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ ከሰለጠኑ የሰው ሃይል ይልቅንስ በአጫጭር ስልጠናዎች፣ በቴክኒክ እና ሞያ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ይቀጥራሉ ይህ ደግሞ ጤናማ ነው ብለዋል።

በኢኮኖሚው ላይ ተፈላኪ ያልሆኑ የት/ርት ክፍሎችን በበቂ ጥናት በመደገፍ ት/ት ክፍሎቹ እንዲዘጉ እና መንግስት ቁልፍ የኢኮኖሚ እድገት ምንጭ ናቸው ባላቸው አምስት ዘርፎች ላይ ማለትም በቱሪዝም፣ በማኒፋክቸሪንግ፣ ግብርና፣ ማዕድን፣ አይሲቲ ላይ በበቂ ሁኔታ በማሰልጠን እንዲሁም የጉልበት ገበያ ስራታችንን ማዘመን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል ያሉት ሚኒስቴር ዲኤታው ለዚህም ደግሞ ዩንቨርስቲዎችን በተለእኮ እና በፕሮግራም እንዲቃኙ የማስቻል ስራ እየሰራን ነው ብለዋል።

በማህሌት አማረ
2022-12-13