ሀገሬ ቲቪ

የአውሮፓ ኀብረትን ያላስማማው ውይይት

የአውሮፓ ኀብረት በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ውይይት ቢቀመጥም ሳይስማማ ቀረ። ኀብረቱ ማዕቀብ ለመጣል ያቀደው በ 200 ግለሰቦች፣ ኩባንያዎች፣ ሦስት ባንኮች እንዲሁም የማዕድን እና የኃይል ኢንዱስትሪዎች ላይ ነበር።

የኀብረቱ አባላት በዘጠነኛው ጥቅል ማዕቀብ ላይ ግን መግባባት እንዳልቻሉ ተሰምቷል።

በማዕቀቡ ይዘቶችና ሊኖረው በሚችለው ተጽዕኖ ላይ አለመግባባት እንደነበረ የኅብረቱ የውጪ ጉዳይ ሹም የኾኑት ጆሴፍ ቦሬል ተናግረዋል። ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-13