
ኬኒያ የነጽነት ቀኗን አከበረች። ሀገሪቱ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችበትን 59ኛ ዓመት ነው ያከበረችው።
በክብረ- በዐሉ የተገኙት አምስተኛው የኬኒያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ነጻነታችንን መቀዳጀታችን በርካታ ስኬቶችን አስገኝቶልናል ብለዋል።
ሩቶ ኬንያ በአፍሪካ ውስጥ ፀጥታና መረጋጋት እንዲሰፍን በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ ቁርጠኛ ናት ብለዋል።
በቀጠናውም ቢኾን ለሰላም ደኀንነት እና መረጋጋት እንዲሰፍን የጠነከረ አመራር በማስመዝገባችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-12-13