ሀገሬ ቲቪ

በአዲስ አበባ ለተፈጠረው ሁከት የከተማ አስተዳደሩ ተጠያቂ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጦች ከተማ መስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል አለ።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በከተማዋ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ሰንደቅ አላም እና የኦሮሚያ ክልል መዝሙር ተማሪዎች በማስገደድ እንዲዘምሩ እያደርጉ የሚገኙት ግለሰቦች እና የመንግስት ባለስልጣናት ናቸው በሏል።

በከተማዋ ትምህርት ቤቶች የሚደርጉ ማናቸውም ተግባራት የከተማዋን ፍቃድ እና የሁኝታ ማገኘት ይገባቸዋልም ብሏል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-13