ጆ ባይደን የአፍሪካ ዜጎችን በዲጂታል ኢኮኖሚው ዘርፍ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ የ350 ሚሊዮን ዶላር ዕቅድን ይፋ አደረጉ።
በአፍሪካ-አሜሪካ የቢዝነስ ፎረም ላይ ባይደን ይፋ ያደረጉት ዕቅድ አምስት ሚሊዮን አፍሪካውያን የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል ተብሏል።
እቅዱ በዋናነት አፍሪካውያን በዲጅታል ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲሳተፉ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል። በዚህ ሂደት ማይክሮሶፍትና ቪያሳት የተሰኙ የኢንተርኔት አቅራቢ ድርጅቶች የሚሳተፉ ይሆናል።
በአብርሃም በለጠ
2022-12-16
