ሀገሬ ቲቪ

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ

በጎንደር ከተማ በተፈጠረው ግጭት የተሳተፉ ግለሰቦችን አድኖ ወደ ህግ ለማቅረብ እየተሰራ እንደሆነና እስካሁንም በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ የሃይማኖት ግጭት እንዲቀሰቀስ እየሰሩ ያሉ ኃይሎች እንዲያቆሙ አሳስበዋል፡፡ በሌላ በኩል በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የተከሰተው ድርጊት ሊወገዝ የሚገባው አጸያፊ ተግባር ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው እኩይ ተግባራቸውን ለመፈጸም የሞከሩ ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ወደ ወራቤ አካባቢ ግጭቱን ለማስፋፋት የተሞከረው የተናበበ እንቅስቃሴ የእስልምናንም ሆነ የክርስትናን እምነት አይወክልም ብለዋል ።

በሀገሬ ቲቪ
2022-04-29