በአንድ ሃገር ተአማኒ እና የተደራጀ መረጃ መኖር በመንግስት እና በህዝብ መሃከል ያለውን መተማመን ከማሳደግ አንጻር ሚናው ከፍተኛ ነው ።
ታማኒ መረጃን ለህዝብ ከማድረስ አንጻር ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ሚናቸው ትልቅ ነው። ነገር ግን እነዚሁ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ተአማኒ መረጃን ለዜጎች ለማድረስ በሚያደርጉ ጥረቶች ከመንግስት የመረጃ ሰጪ ባለሞያዎች መረጃ በአግባቡ እየተሰጠ እንዳልሆነ ያንጋገርናቸው ጋዜጠኞች ተናግረዋል ።
በኢትዮጲያ የመገናኛ ብዙኃን እና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ከወጣ 12 አመታትን አስቆጥሯል ። ይህን አዋጅ ተፈጻሚ እንዲሆን የሚያደርገው ተቋም ደግሞ የኢትዮጲያ ህዘብ እንባ ጠባቂ ተቋም ነው ።
አዋጁ ዜጎች እና የመገናኝ ብዙሃን ባለሞያዎች መረጃን በነጻነት የማግኘት መብት እንዳላቸው የሚገግለጽ ቢሆንም መንግስት እና የግል ተቋማት ግን መረጃ ለመገናኛ ብዝኋን ባለሞያዎች ሲሰጡ አይሰተዋልም። ነገር ግን የመረጃ ነጻነት አዋጁ የመንግስት አስፈጻሚዎችን የሚጠይቅ ህግ ባለ ማስቀመጡ ለመቆጣጠር አለመቻሉን የኢትዮጲያ ህዘብ እንባ ጠባቂ ተቋም ይገልጻል።
የመገናኛ ብዙኃን እና የመረጃ ነፃነት አዋጁ ለ ዜጎች እና ለመገናኛ ብዙህን መረጃን እንዲያገኙ መብት ቢያጎናጸፈም ዛሬም ድረስ መገናኛ ብዙሃኑ መረጃን ለማግኘት እየተፈተኑ ይገኛሉ።
ዜጎች በሃገሪቱ ውስጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን እንዲመለከቱ እና እንዲሰሙ የማድረግ ተግባራትን የሚከውኑት የመገናኛ ብዙህን ናቸው ። እኚሁ የመገናኝ ብዙሃን ባለሞያዎች መረጃን ለማግኝት ያደረጉትን ጥረት አለመሳካቱን ለዜጎች በተግባር ማሳየት የገባቸዋል ተበሏል ።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-16
