የሃገራት የተረጋጋ ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ፣ ያላቸውን የተፈጥሮ ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም ፣ እንዲሁም የደህንነት ሰጋታቸውን ለመቅረፍ ከ 1950 ጀምሮ በህዋ ሳይንስ ፉክክር ወስጥ ይገኛሉ ።
በአለም የህዋ ምህዋር ወስጥ ከ6ሺ በላይ ሳታላይቶች ይገኛሉ ። ከ70 በላይ ሃገራት ደግሞ የነዚሁ ሳተላይቶች ባለቤቶች ናቸው።
ሳተላይቶች በዘመናዊ ቲክኖሎጂዎች እየተሻሻሉ ሄደው በ1965 የሪሞት ሴንሲንግ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ። ከዚህ በኋላ ተለያዩ ሪሞት ሲስንሲንግ ሳተላይቶች ወደ ምህዋር መጠቀዋል ።የአፍሪካ ሃገራትም ከ40 በላይ ሳተላይቶች ማምጠቅ ችለዋል ።
ኢትዮጲያም ለራሷ የመጅመሪያውን ለምስራቅ አፍሪካ ደግሞ ሶስተኛውን የሆነውን ETRSS 01 የተባለች ሪሞት ሴንሲንግ ሳተላይት ወደ ህዋ ያመጠቀችው በዛሬው ቀን ከ ሶስት አመት በፊት ነበር።
የሳተላይቷ ግንባታ 2008 ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በፈረሙት ስምምነት መሠረት በቻይና መንግስት ትብብር የተጀመረ ነበር ።
የሳተላይቷ ጠቅላላ ክብደት 72 ኪሎ ግራም የመተመዝን ሲሆን በተወነጨፈች በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የህዋ የምሕዋር ቦታዋን ይዛለች።
የሳተላይት ግንባታ ወጪዋ በቻይናና የኢትዮጵያ መንግስት በጀት የተሸፈነ ሲሆን ለዲዛይን እና ለግንባታው ሁለት መቶ 10 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ ተደርጎባታል ።በግንባታው ከቻይና ሳይንቲስቶች በተጨማሪ 21 የሚደረሱ የኢትዮጲያ የስፔስ ባለሞያዎች ተሳተፈዋል ።
ወደ ምህዋር የመጠቀችው ሳተላይቷ የምትሰጠው አገልግሎት ለግብርና መረጃ፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመገናኛ ቴክኖሎጂና ለመሳሰሉት ነው፡፡
ሳተላይቷ በህዋ ቆይታዋ ለምትልካቸው መረጃ መቀበያ ጣቢያ እንዲሆን በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ተቋም ወስጥ የተገነባ ሲሆን የሳተላይቷን የቁጥጥር ስራ እየሰሩ የሚገኙት አትዮጲያዊያን ናቸው።
በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-19
