ሀገሬ ቲቪ

አፍሪካ ሰላማዊ የምርጫ ዓመት አሳልፋለች

በፈንጆቹ 2022 አፍሪካ ሰላማዊ የምርጫ ዓመትን ብታሳልፍም መፈንቅለ መንግስት እና ድርቅ አሁንም ፈተና ኾነውባታል ተባለ።

ለአምስተኛ ጊዜ የተከሰተው የዝናብ እጥረት ምሰራቅ አፍሪካን ዳግም ለድርቅ እና ለከፋ ረሀብ ሲያጋልጣት፤ በምዕራብ አፍሪካ ዛሬም ድረስ ጉልበታቸው እየፈረጠመ የመጣው አሸባሪዎች እያደረሱ ያለው ጥቃት ለአፍሪካ ዓመቱን አክፍቶባታል።

የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ደግሞ ለለጋሽ ሀገራትን ፊታቸውን ከአፍሪካ አንስተው ወደ ዩክሬን ማዞራቸው፤ አህጉሪቱ ክፉ ግዜዋን ማለፊያ ድጋፎችን ከለጋሾቹ እንዳታገኝ እንቅፋት ሆኖባታል ነው የተባለው።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-19