ሀገሬ ቲቪ

የላይቤሪያ ዜጎች አደባባይ ወጡ

የላይቤሪያ ዜጎች በፕሬዙዳንት ጆርጅ ዊሃ ላይ ተቃውሟቸውን አሰሙ።

የዋጋ መናር እና የመሠረታዊ ፍጆታዎች እጥረት ሰልፈኞቹ አደባባይ ለመውጣታቸው ምክንያት ነው ተብሎለታል።

ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ መንበረ ስልጣኑን ሲይዙ በሀገሪቱ ያለውን የኑሮ መወደድ ለማስተካከል ቃል ገብተው ነበር።

ሰልፉን ካስተባበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ የአንደኛው መሪ፤ ፕሬዚዳንቱ እንደህዝብ ተፈትነው ወድቀዋል፣ ያሉትን ማድረግ አልቻሉም ሲሉ ተደምጠዋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-12-19