በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የኢትዮጵያ ቡና ኤግዚቢሽንን ተደረገ።
የቡና ትዕይንቱ የእንግሊዝ እና ዓለም አቀፍ የቡና ገዥዎች እና አቀነባባሪዎች ከኢትዮጵያ የተቀነባበረ ቡና አቅራቢዎች ጋር በመተባበር የተካሄደ ነው።
በኤግዚቢሽኑ ላይ አምባሳደር ዉብሸት ደምሴ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ እንደመሆኗ ይህ አይነት የንግድ ግንኙነት አስደሳች ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የቡና ማህበር ተወካይ ሚኒሊክ ሀብቱ በበኩላቸው ብልዩ ጣዕሙ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ ቡናን በማስተዋወቅ በኩል ሁነቱ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-12-19
