ሀገሬ ቲቪ

የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ከታህሳስ 13 ጀምሮ ይሰጣል

በአምስት ክልሎች የተከሰተውን የኩፍኝ በሽታ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተቀናጄ የኩፍኝ ክትባት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በመደበኛ የጤና ተቋማት እንዲሁም በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ተቋማት ከታህሳስ 13 እስከ 22 ይሰጣል።

ከክትባቱ ጎን ለጎን የህፃናትን ሞት ለመቀነስ የስርአተ ምግብ ልየታ፣ የቫይታሚን ኤ ጠብታ እደላ፣ የአንጀት ትላትል መከላከያ መድሀኒት እደላ እንዲሁም ከወሊድ ጋር የተያያዘ የፊስቱላ ህመም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እንደሚሰሩ የጤና ሚኒስተር የኩፍኝ በሽታ ክትባትን አሰመልክቶ ለሚዲያ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረከ ላይ ገልጿል።

በማህሌት አማረ
2022-12-19