ሀገሬ ቲቪ

ሮኬት ያስተናገዱት ጉተሬዝ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኪዩቭን በመጎብኘት ላይ ሳሉ የአየር ጥቃት ደረሰ። በአየር ጥቃቱ በዋና ፀሐፊው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ተናግረዋል። ነገር ግን ሦስት የሀገሬው ነዋሪዎች ተጎድተው በህክምና ላይ እንደሚገኙ የኪዬቭ ከንቲባ አስታውቀዋል። ጉቴሬዝ በጉብኝታቸው ወቅት ድርጅታቸው የዩክሬንን ጦርነት ማስቆም ተስኖታል ያሉ ሲሆን ይህም እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል ።

በሀገሬ ቲቪ
2022-04-29