
የጸደይ አብዮት በመባል የሚታወቀው የአረብ አብዮት መጀመሪያዋ ቱኒዚያ የዘመናት ገዥዋን ቤን አሊንን አስወግዳ አመጿን ብታጠናቅቅም የተረጋጋ መንግስት የመመስረቱ ሂደት ግን አሁንም አላለቀም የሚሉ አሉ።
የ2011 የአርብ አብዮት ባመጣው ነውጥ እስካሁንም ድረስ ከሚታመሱት ሀገራት አንጻር መረጋጋት ያላት ብትሆንም ያአመጹ አስነሺ ቡአዚዝ ጥያቄዎች አሁንም አልተመለሱም።
ስርአጥነት ዪኢኮኖሚ አለመረጋጋት ሙስና ቱኒዚያውያን አሁንም በጥያቄነት የሚያነሱት ጉዳይ ነው ። የወቅቱ ፕሬዘዳንት የህግ ፕሮፌሰሩ ካዪ ስይድ ወድ ስልጣን ሲመጡ በተለይ በሙስና ላይ ጠንከር ያለ ዘመቻን እንደሚወስዱ ቢዝቱም የተሳካላቸው አይመስልም። ከሳቸው ይልቅ ተቃውሚዎቻቸው የቱኒዚያን ልብ ያገኙ ይመስላል።
አምስት ተቃዋሚዎች በጋራ ሆነው ባለፈው ቅዳሜ በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ ላይ እንደማይሳተፉና ህዝቡም ለምርጫ እንዳይወጣ ያቀረቡት ጥያቄ ሰምሮላቸዋልና።
ምክንያቱም ለመራጭነት ከተመዘገበው 9 ሚሊየን መራጭ የወጣው 9 በመቶው ብቻ የሚጠጋ ነው።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪ ቼቪ ይህ ለፕሬዘዳንት ሳይድ ከከፍተኛ መሬት መንቅጥቀጥ አይትናንነስም ህዝቡ በሚገባ እንደማይፈልጋቸው አርጋግጧል የእኛንም ቃል ሰምቷል ብለዋል። ከዚህ በኋላ ህጋዊ ፕሬዘዳንት ነኝ ሊሉ የሚችሉበት ምንም መሰረት ያላቸውም ነው ያሉት ።
የሃገሪቱ ምርጫ ቦርድ ይህ በታሪክ ታይቶ ይማይታወቅ አንስተኛ የመራጭ ቁጥር እንደሆን አስታውቋል።ፕሬዘዳንቱ ግን እስካሁን ያሉት ነገር የለም ።ምናልባት ከስልጣን የመውረዱን ጥያቄ ካሂ ስይድ የማይቀበሉት ከሆን ግን ተቃዋሚዎች ህዝቡ ለአመጽ ወደ አደባባይ እንዲውጣ ሊያደርጉት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
በብሩክ ያሬድ
2022-12-19