ሀገሬ ቲቪ

የአስኮ አዲስ ሸማቾች ማኀበር አባላት ቅሬታ

1999 ዓ.ም የተመሠረተው የአስኮ አዲስ ሰፈር ሁለገብ ሸማቾች የኀብረት ሥራ ማኀበር ለበርካታ ዜጎች አገልግሎትን ሲሰጥ ከቆየበት ይዞታው እንዲነሳና ትእዛዝ መተላለፉን እና አገልግሎት መስጫ ሱቆቹ ከጥቅምት 30 ጀምሮ እንደታሸገቡት የማኀበሩ የቦርድ አመራር እና ሰራተኞች ቅሬታቸውን ለጣቢያችን ገለጸዋል።

ከዚህ ቀደም በአካባቢው ጤና ጣቢያ ባላመኖሩ ለጤና ጣቢያ ግንባ ቦታ ሲፈለግ ማኀበሩ የያዘው ቦታ ሰፊ እና በቂ በመኾኑ በስምምነት በግቢው ውስጥ ጤና ጣቢው ተገንብቷል።ይኸው ጤና ጣቢያ ወደ መጠናቀቁ ሲቀርብ ግን ከቦታው እንዲለቁ መታዘዛቸውን ተናግረዋል።

የማኅበሩ አባላት ከወረዳ 14 ኃላፊዎች ጋር ስለምትክ ቦታ እና ተያያዥ ጉዳዩች ተወያይተው ምላሽ እንደሚሰጡዋቸው ቢነጋገሩም ይህ ሳይኾን የወረዳው ማኀበራት ማደረጃ አማካይነት ሱቆቹ እንዲታሸጉ ተደርገዋል።

ሸማች ማኀበሩ የታሸገበት መንገድ አግባብ ባለመኾኑ አቤቱታዎችን ባለማግኘታችን ወደ ክስ አምርተናል ያሉን ደግሞ የማሕበሩ የቦርድ አባል አቶ ግዛው ደበሌ በሸማች ማኀበሩ ስጋቤት፣ የሸቁጥ ሶቆች እና ወፍጮ ቤት ውስጥ ያሉ የሚበላሹ ምርቶች፣ የደሞዝ መክፈያ ሰነድ ሳይወጡ ጭምር መታሸጉ በሰራተኛው እና በደንበኞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ደንበኞች እና ሠራተኞች ነግረውናል።

ወረዳ 14 እና የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የማኀበራት ማደረጃ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-19