ሀገሬ ቲቪ

በማላዊ 245 ኢትዮጵያውያን ከእስር ሊፈቱ ነው

መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲጓዙ በማላዊ ተይዘው በእስር ላይ የነበሩ 245 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገቸው ሊመለሱ ነው።

ኢትዮጵያውያኑ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ማላዊን ሲያቋርጡ በቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው።

በማላዊ ሞተው የተገኙትን 27 ኢትዮጵያውያን ናቸው የተባሉ ሰዎችን ጉዳይ ለማጣራት ወደ ማላዊ ደርሶ የተመለሰው አጣሪ ቡድን ጥረት ነው ሊፈቱ የቻሉት።

ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘም የማላዊ መንግስት 6 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለም ተሰምቷል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-12-19