ኢትዮጵያ ከስጋ ምርት ከ41 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሬ አገኘች።
የግብርና ሚንስቴር እንዳለው ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ወራት ስጋን ወደ ውጪ በመላክ 41.8 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማኘት ችላለች።
ገቢው ከ5 ሺሕ 900 ቶን በላይ የስጋ ምርትን በመላክ የተገኘ ነው። ከሰኔ 30 2014 ዓ.ም. ጀምሮ 25 ሺሕ ኪሎግራም በላይ ስጋን ወደውጪ መላክ ተችሏል።
ሀገሪቱ ከ200 ሺሕ ቶን ሥጋ በላይ ለዓለም አቀፉ ገበያ የማቅረብ አቅም እንዳላት የጠቆመው መስሪያ ቤቱ ይህንን አቅሟን ለመጠቀም እየሰራ መሆኑን የዘገበው አፍሪካን ኒውስ ነው።
በሳምሶን ገድሉ
2022-12-20
