ሀገሬ ቲቪ

የአውሮፓ ኀብረት ለኢትዮጵያ የ1.8 ቢሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የአውሮፓ ኀብረት ለኢትዮጵያ በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች የትምህርት ተቋማት እና ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራሞቻቸው የሚውል የ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ህብረቱ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን የትምህርት አገልግሎት ለመመለስ ድጋፉን ያደረገው ከዩኒሴፍ እና ከዓለም አቀፉ የምግብ ተቋም (WFP) ጋር ባለው ትብብር በኩል ነው።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮብያ በጦርነት ውስጥ ህጻናት ንጹህ ተጎጅዎች ናቸው፤ ያሉ ሲሆን ፣ በጦርነት ምክንያት በኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን አስታውሰዋል።

በጦርነቱ 8 ሺህ 500 ት/ቤቶች የተለያየ ጉዳት ያሰተናገዱ ሲሆን 1 ሺህ 500 የሚሆኑት ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-12-20