ሀገሬ ቲቪ

ከእንስሳት የሚተላለፍ ቫይረስ

የአየር ንብረት ለውጥ ከዱር እንስሳት ወደ ሰው ልጆች የሚተላለፉ ቫይረሶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረው ነው ሲሉ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት የአየር ሙቀት መጨመር አጥቢ እንስሳት መኖሪያቸውን ለቀው እንዲሄዱ ያስገድዳቸዋል። ታዲያ እነዚሁ እንስሳት በስደታቸው ወቅት ከሰው ልጆች ጋር በመገናኘት ቫይረሶችን በቀላሉ ያስተላልፋሉ። በዚህም ሳቢያ በፈረንጆቹ 2070 15 ሺሕ አዳዲስ ቫይረሶች በእንስሳት አማካኝነት የሰው ልጆችን ሊጎበኙ ይችላሉ ሲል ኔቸር በተሰኘ መጽሔት ላይ የወጣ ጥናት አመልክቷል።

በሀገሬ ቲቪ
2022-04-29