ሀገሬ ቲቪ

በትግራይ ክልል የባንክ አገልግሎት ተጀመረ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሽረ እንደስላሴና አካባቢው የሚገኙት ቅርንጫፎቹ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታወቀ።

በተመሳሳይ ወጋገን ባንክ በአላማጣና በራያ ጥሙጋ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል።ባንኩ ሰቲት ሁመራ፣ አዲ ረመፅ ፣ ዳንሻ እና ተከዜ ቅርንጫፎች ቀደም ብለው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታውሷል።

በቅርቡ ፤ በመቐለ እና በሽረ ዲስትሪክቶች በሚገኙ ቅርንጫፎች አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቄአለሁ ብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሽረ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተማዎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ የሚላኩ ገንዘቦችን የመቀበል እና ገንዘብ የማስቀመጥ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ማሳወቁ ይታወሳል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-20