በአለማችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የልብ የደም ቧንቧ ቅንጣቶችን በላብራቶሪ በማሳደግ የአንድን እንግሊዛዊ ህፃን ህይወት መታደግ ተችሏል።
ከልብ ህመም ጋር የተወለዱ ህፃናትን ሰው ሰራሽ ልብ ሳይጠቀሙ የሚድኑበት ቴክኖሊጂ ነው የተባለለት ይሄው ቴክኖሎጂ ስራየ ተብለው ለምርምር በላብራቶሪ በተቀመጡ የእንግዴ ልጅ ዘረ መል በመውሰድ ህዋስ በማሳደግ ህክምናው ውጤታማ መሆኑ ተነግሯል።
በአለማችን ላይ ብዙ ህፃናቶች በተለያዩ ምክኒታቶች ከልብ ህመም ጋር አብረው ይወለዳሉ። እነዚህ ህፃናቶች ታዲያ የልብ ህክምናዎች ቢያገኙም ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘትት ደግሞ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ የቀዶ ህክምና ሲያደርጉ ይስተዋላሉ።
ከወደ እንግሊዝ የተገኘው ምርምር ደግሞ በልብ ህመም የሚሰቃዩ ልጆች ከዚህ በኋላ አይኖሩም ያለ ይመስላል። ነገሩ ምን መሰላችሁ እንግሊዝ ሃገር ብሪስቶል ሮያል ሆስፒታል የተወለደው ፊኒሌ የልብ ቧንቧ ችግር አጋጥሞት ነበር። ታዲያ ይህ ህፃን በተወለደ በአራተኛ ቀኑ ቀዶ ጥገና ይደረግለታል።
ነገር ግን ቀዶ ጥገናው ውጤታማ ሊሆን አልቻለም እንዲያውም በግራ ልቡ ላይ የደም ዝውውር ችግር በማጋጠሙ ምክኒያት የልብ እና የሳንባ መተንፈሻ ማሽን አስፈልጎት ነበር።
የህክምና ባለሙያዎቹ የፊኒሌ የልብ ህመም ስላሳሰባቸው አንድ መፍትሄ መዘየድ ግድ ብሏቸው ነበር። ለዚህም ደግሞ ከዚህ በፊት ተሞክሮ የማያውቀውን የልብ የደም ቧንቧ ህዋሶችን እና በላብራቶሪ ከሚያስቀምጡት የእንግዴ ልጅን ዘረ መል በመውሰድ በላብራቶሪ በማሳደግ እና የፊሊ የልብ የደም ቧንቧዎች በራሳቸው ማደግ የሚችሉበት እንደሆነ እምነት ነበራቸው።
ለዚህ ምርምራቸው ውጤታማነት ደግሞ ለንደን ውስጥ የሚገኘው የሮያል ፍሪ ሆስፒታል ተመራማሪዎች የልብ ቧንቧ ህዋሳቶቹን እና ዘረ መሉን በተገቢው መንገድ አሳደጉ።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዋሳቶች በቀዶ ህክምና የተሰጡት ፊኒሌ የልብ ቧንቧ ጡንቻዎቹ እንዲጠነክሩ እንዲሁም ተፈጠረው የነበሩ የደም ቧንቧ ክፍተቶችን በመሙላት በትክክል የደም ዝውውር ስራቸውን እንዲያከናውኑ አድጓቸዋል።
ፊኒሌም በአሁኑ ሰአት ህክምናውን ጨርሶ ጤነኛ ህይወት እየመራ መሆኑንን ቢቢሲ ዘግቧል።
አርቲፊሻል የደም ቧንቧ ቱቦዎች በተደጋጋሚ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋቸዋል። ምክኒያቱ ደግሞ የልጆች አካላዊ እድገት ጋር ተያይዞ በየጊዜው መቀየር ግድ ስለሆነ ነው።
አሁን በእንግሊዝ የተገኘው ይሄው የምርምር ውጤት እና ሰዎችበተለይም ደግሞ ህፃናት የሌሎችን ድጋፍ ሳይፈልጉ ከራሳቸው የልብ ቧንቧ ህዋሳትን በመውሰድ ብቻ በላብራቶሪ እንዲያድግ ተደርጎ መሰጠት መቻሉ በልብ ህመም ለሚሰቃዩት ፍቱን መፍትሔ ነው አስብሎታል።
በማህሌት አማረ
2022-12-21
