ቻይና በዓለም ሁለተኛ የሆነውን የሀይል ማመንጫ ጣቢያ ገንባታ ማጠናቀቋን አስታወቀች።
በያንግዚ ወንዝ ላይ የተገነባው ባሂታን የተሰኘው የሃይል ማመንጫ ጣቢያ 16 ጊጋዋት ሀይል የሚያመነጩ ተርባይኖች የተገጠመለት ሲሆን ይህም በዓለማችን ሁለተኛው ግዙፍ ሀይል ማመንጫ ጣቢያ አድርጎታል።
ፕሮጀክቱ በሰዓት 62.44 ቢሊዮን ኪሎዋት ሀይል የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል ። በዓመት 90.45 ሚሊዮን ቶን የሚሆን የድንጋይ ከሰል በመቆጠብ በየዓመቱ የሚወጣውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን በ248.4 ሚሊዮን ቶን መቀነስ እንደሚችልም ተነግሯል።
ሀገሪቱ ይህን ጣቢያ ለማስገንባት 24.38 ቢሊዮን ዶላር አውጥታለች ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-12-21
