የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዓለም አቀፉ ወረርሽኝ በፊት የነበረው የተጓዦቹ ቁጥር እንደሚመለስ አስታወቀ።
የአየር መንገዱ ኃላፊ መስፍን ጣሰው መዳረሻዎቹን እና አውሮፕላኖቹን በመጨመሩ ብሎም በሰላም ስምምነቱ፣ በዚህ በጀት ዓመት የተጓዦቹ ቁጥር እንደሚያድግ ገልጸዋል። ከወረርሽኙ በፊት 12.1 ሚሊዮን ተጓዦች በዓመት ያጓጓዘው አየር መንገዱ፣ ባለፈው ዓመት 8.6 ተጓዦችን ነው ማጓጓዝ የቻለው።
በዚህ በጀት ዓመት 12.7 ሚሊዮን ተጓዦችን ዓየር መንገዱ ያጓጉዛል ብለው እንደሚጠብቁ ኃላፊው መስፍን ጣሰው ገልጸዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-12-21
