ሀገሬ ቲቪ

አፍሪካዊው ቼኩ ቬራ ቶማስ ሳንካራ የተወለደበት ቀን

አፍሪካ ዘመናት በቀኝ አገዛዝ ሰንሰለት አሳልፋ በ1950ዎቹ መጨረሻ ከባርነት አገዛዛ ብትወጣም ፣ ስልጣን የጠማቸው የራሷ ዜጎች ለዘመናት አሰቃይተዋታል ።

ከቅኝ ግዛት በኋላ ግን በምዕራብ አፍሪካ ለአራት አመታትም ቢሆን ዲሞክራሲ ፣ ሰላም ፣ልማት ጮራ ፈንጥቆ ነበር ለዚህ ጮራ መፈንጠቅ ምክንያቱ ደግሞ ሻምበል ቶማስ ሳንካራ ነው ።ይህ ጀግና የተወለደው በ1942 ዓ.ም ከዛሬ 75 አመት በፊት በዛሬው ቀን ነበር ።

ቶማስ ሳንካራ የተወለደው በሰሜን አፐር ቮልታ በአሁኗ ቡርኪናፋሶ ውስጥ ነው ። ቶማስ ለቤተሰቡ 3ተኛ ልጅ ነው ።አፐር ቮልታ ማለትም ቡርኪናፋሶ በፈርንሳይ ከቀኝ አገዛዝ ነጻ በወጣችበት ወቅት ቶማስ ሳንካራ የ 12 አመት ልጅ ነበር ።

ሃገሪቱ ከፈርንሳይ አገዛዝ ነጻ ከወጣች በኋላ ለ 17 አመታት ለ 4 ግዜ መፈንቅለ መንግስት ተካሂዶባታል ።ቶማስ ሳንካራ በተደጋጋሚ ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት የተሰቃየችወን ሃገሩን ለመታደግ በ17 አመቱ ወደ ወታደራዊ አካዳሚ ተቀላቀለ ።

በወታደራዊ አካዳሚው ጥሩ ወጤትን ያስመዘገበው ቶማስ ሳንካራ ፣ ለተሻለ ወታደራዊ ትምህርት ወደ ማዳጋስካር ተላከ ። ከዛም በኋላ ሞሮኮም ሄዶ ወታደራዊ ትምህርትን አጥንቷል ። ሳንካራ በወታደራዊ እውቀት ብቻ እራሱን አላበቃም በፖለቲካ እወቀትም እራሱን ያደረጀ ነበር ።

ቶማስ ሳንካራ ወደ ሰልጣን ከመምጣቱ በፊት ሃገሩን በማስታወቂያ ሚንስቴርነት አገልግሏል። ከዚያ በኋላ በ1976 ቶማስ ሳንካራ ፕሬዝዳንት ሆነ ።

ቶማስ ወደ ሰልጣን መንበር እንደወጣ የመጀመሪያ ተግባሩ የነበረው አፕር ቮልታ የሚለውን የሃገሪቱን ስም ወደ ቡርኪናፋሶ መቀየር ነበር ትርጉሙም የቀጥተኛ ሰዎች ወይንም የትክክለኞች ሃገር ማለት ነው ።

ቶማስ ሳንካራ ወደ ሰልጣን ከወጣ በኋላ ሙሰኛ የሃገሪቱ ዜጎችን ወደ ፍርድ አቅርቧል፣ የሚንስቴሮች ተንደላቀቀ ህይወትን መስመር እንዲያዝ አደርጓል፣ ሴቶችን ወደ ስልጣን አምጥቷል።

በሃገሪቱ የነበረን የጤና ሽፋን ከ 6% በአራት አመት የስልጣን ቆይታው ወደ 20% አሳደጓል ። የሃገሪቱ ዜጎች ከእርዳታ ምግብ በማውጣት ሁሉም ዜጋ እንዲመገብ አስችሏል ። በሳንካራ የስልጣን ዘመን በሃገሪቱ የሚገኙ ማንኛወም ሚንስቴር እና ሰራተኞች ቡርኪናፍሶ ያመረተችውን ልብስ እንዲለብሱ እና ከአውሮፓ የሚመጣን ምንም አይነት ቁሰን እንዳይጠቀሙ አዞ ነበር ።

ቶማስ ሳንካራ በ1987ቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠንካራ ሃሳቦችን በማሳትም ይወሳል ።ሳንካራ በሰብሰባው በቀኝ ግዛት ሲመዘብሩን ለነበሩ ገዢዎች የብድር እዳን መክፈል የለብንም ፣ ለብዙ አመታት ሃብቶቻችህንን መዝብረውናል ሰልዚህ አንከፍልም ብለን ልንቆም ይገባል ሲሉ ተናግረው ነበር በወቅቱ በሰብሳብ የነበሩ መሪዎች የስንካራን ሃስብ በሳቅ አጣጥለወታል ።

ሳንካራ ሃገራት እራሳቸውን መቻል አለባቸው የሚል ሃሰብ ደስ ያልተሰኙት ምዕራባዊያን ሃገራት የሳንካራን እንቅሰሳሴ በጥንቃቄ ከተመልከቱ በኋላ ምዕራባዊያኑ ባቀነባባሩት መፈንቅለ መንግስት አፍሪካዊ ቼኩቬራ ቶማስ ሳንካራ እንዲገደል አደረጉ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-21