ሀገሬ ቲቪ

የኢቦላ ቫይረስ ያሳደረው ስጋት

ታንዛኒያ የኢቦላ ቫይረስ በእጅጉ አስግቶኛል አለች በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አዲስ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ተከትሎ ታንዛኒያ ስጋቷን ገልጻለች ቫይረሱ ወደ ታንዛኒያ እንዳይገባ የሀገሪቱ የጤና ሹማምንት በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከኮንጎ ጋር በምትዋሰንባቸው ድንበር ምርመራ እና ክትትል የሚያደርጉ የጤና ባለሙያዎች ተልከዋል። የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር የኢቦላ ቫይረስ እንደ አዲስ መከሰቱን ከሰማን ጀምሮ ወደ ታንዛኒያ እንዳይሰራጭ እየተጋን ነው ብሏል። በሰሜን ምዕራብ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በምትገኘው ምባንዳካ ከተማ የቫይረሱ ዳግም ተክስቶ የሁለት ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 267 ሰዎች በኢቦላ ቫየርስ መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ማስታወቁን የሲጂቲኤን ዘገባ አስታውሷል

በሀገሬ ቲቪ
2022-05-03