ሀገሬ ቲቪ

አፍሪካ ከአረንጓዴ ሃይድሮጅን ሽያጭ 1.1 ዶላር ልታገኝ ትችላለች ተባለ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ባወጣው አዲስ ሪፖርት አፍሪካ ከአረንጓዴ ሃይድሮጅን ሽያጭ 1.1 ትሪሊዮን ዶላር ልታገኝ ትችላለች ብሏል።

በ2035 የአፍሪካ የፀሐይ ኃይል በመጠቀም በዓመት 50 ሚሊዮን ቶን አረንጓዴ ሃይድሮጅን በማምረት የአለም አቀፍ የሃይል ፍላጎትን ማሟላት አቅም አላት ብሏል ።

የአለም አቀፉ የሶላር ሕብረትና አፍሪቃ ኅብረት ባካሄዱት ጥናት በሞሪታንያ፣ በሞሮኮ፣ በደቡባዊ አፍሪካ እና በግብፅ የሚስተዋለው የጸሃይ ሃይል አረንጓዴ ሃይድሮጅን ለማምረት እንደሚረዳ ተገልጿል ።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-23