ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ ጊዜአዊ የመኖሪያ ፍቃድ ማብቂያ ጊዜን አራዘመች

በኢትዮጵያ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ተሰደው ወደ አሜሪካ ለገቡ ኢትዮጵያውን ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ለተጨማሪ 18 ወር ይራዘማል ተባለ።

ከፈረንጆቹ ታኀሳስ 12 እስከ ሰኔ 2024 ድረስ በልዩ ዕድል ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንደሚራዘም ተነግሯል። በዚህ ዕድል ከ26 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው የተነገረው።

ይህ ዕድል የሥራ ፈቃድም እንደሚያካትት ተገልጿል ።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-23