ሀገሬ ቲቪ

አፍሪካ ኅብረት የሰየማቸው አሸማጋዮች መቀሌ ሊጓዙ ነው

የሰላም ስምምነቱን አተገባበር ለመታዘብ አፍሪካ ኅብረት የሰየማቸው አሸማጋይ ቡድን በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ መቀሌ እንደሚጓዙ ተገለጸ። የቀድሞ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ናቸው ይህን የተናገሩት።

በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት የሰላም ስምምነት ረገድ ብዙ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑንም ተናግረዋል። የህውሓት እና የፌደራል መንግሥት ተወካዮች እና የጦር ኃላፊዎች በድጋሜ በኬኒያ ተወያይተዋል።

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሠላም ሥምምነት አተገባበር አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

በብሩክ ያሬድ
2022-12-23