ይህ ታሪክ መቼም ከማይረሳቸው የሰው ልጅ ፅናቶች መካከል አንዱ ነው።
መነሻውን ከዩራጓይ ያደረገው የአየር ኃይል ቻርተርድ አውሮፕላን መጨረሻው የቺሊ አየር ማረፊያ እንዲሆን አስቧል።
ያሳፈራቸው ደግሞ በግዜው የሀይስኩል ተማሪ የነበሩ የራግቢ ተጫዋቾች ናቸው። እነዚህ አፍላ ወታቶች የሶሻል ፉትቦል ውድድርን ለማድረግ ቸኩለዋል።
አንዳንዶቹ ቤተሰቦቻቸውን ጭምር ወደ ግጥሚያው ለመውሰድ ጋብዘዋቸው አብረው በቻርተርድ አውሮፕላኑ ተሳፈሩ።
ግዜው ጥቅምት 2 1965 ዓ.ም.፤ ተጫዋቾቹን እና ሌሎች ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ 40 ተሳፋሪዎችን ከ5 የበረራ ባለሙያዎች ዳር ያሳፈረው አውሮፕላን ከዩራጓይ ዋና ከተማ ሞንቶቢዴኦ ተነሳ።
አውሮፕላኑ መብረር እንደጀመረ መጥፎ የአየር ሁኔታ ሊያላውሰው አልቻለም። አርጀንቲና ሞንዶዛ ማረፍ የግድ አለው፤ በማግስቱ ከሞንዶዛ አውሮፕላኑ ተነሳ፤ መጨረሻው ግን ቺሊ ሊሆን አልቻለም።
ከሜንዶዛ የተነሳውን አውሮፕላን እያበረረ የነበረው ፓይለት ተመሳሳይ በረራዎችን ለ29 ግዜያት አድርጓል። 30ኛው ግን እንዳሰበው አልሆነም።
በአርጄንቲና እና ቺሊ ድንበር ላይ ያሉ ተራሮችን ለማቋረጥ በሚተበቅበት ከፍታ ልክ እንዳለ ያሰበው አብራሪ አውሮፕላኑን ሲያዞር ከአርጀንቲና አልወታም ነበር።
አውሮፕላኑን ዝቅ ያደረገው አብራሪ በጉም የተሞሉ የአርጀንቲና ጠረፍ ተራሮችን በመጨረሻ አስተዋለ፤ ግን ምንም ማድረግ ሳይችል ቀረ።
አውሮፕላኑ በበረዶ በተሸፈነ ተራራ ስር ወደቀች። 12 ሰዎች ወዲያውኑ ሞቱ 33ቱ ብቻ በህይወት መትረፍ ቻሉ።
ማንም ያሉበትማወቅ አልቻለም። 1፣ 2፣ 3 ቀናቶች ተቆጠሩ በዚያ የበረዶ ምድር የሚበላ እና የሚጠጣ በሌለበት ሳምንታት አለፍፉ።
በ18ተኛው ቀን በእኩለሌት የበረዶ ናዳ በነዚያ ተማሪዎች ላይ ተከመረ። በህይወት እያሉ በበረዶ ስር ተቀበሩ። ከዚያ የበረዶ ናዳ 19 ብቻ ቀሩ።
ከአደጋው ከ(60) ቀናት ማለትም ከ2 ወራት በኋላ እርዳታን ፍለጋ 2ቱ ተመርጠው ተነሱ። በእግራቸው በርካታ ተራሮችን ወጡ ወረዱ ለተስፋ እንኳን የሚሆን ነገር መመልከት አልቻሉም።
ጉዟቸውን ከጀመሩ ከ12 ቀናት በኋላ በተራሮቹ ግርጌ ባለ አንድ ወንዝ ዳርቻ ላይ ደረሱ በዚያ ወንዙን ተሻግሮ ላገኙት ገበሬ የደረሰባቸውን አጫወቱን።
ከ72 ቀናት በኋላ ከ50 ዓመታት በፊት በ1965 ዓ.ም. በአደጋው ጠፍተዋል የተባሉትን ሰዎች ማትረፍ ተቻለ። በግዜው ከ40ዎቹ የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ውስጥ 16ቱ ብቻ በህይወት ተገኑ።
በዚያ ለሰው ልጅ የሚከብዱ ነገሮች ሆነውበታል። የሰው ልጅ ቀንን ለመሻገር ነገን ለመኖር ከህሊናው ተጣልቷል።
ሁሉም ከ50 ዓመታት በፊት በአርጀንቲና በረዷማ ተራሮች መሀል ሆነ።
በሳምሶን ገድሉ
2022-12-23
