ሀገሬ ቲቪ

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ምታደርገው ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጠየቀች

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የምታደርገው ጦርነት እንዲያበቃ ፍላጎቴ ነው አለች። ፕሬዝዳንት ቭላድ ሚር ፑቲን በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ንግግር ያለውን ችግር በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍታቱ የተሻለ ነው ብለዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ወደ አሜሪካ በማቅናት ከአቻቸው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር መምከር ከጀመሩ በኋላ ነው ፑቲን ችግራችንን በሰላም እንፍታ የሚል ንግግራቸውን ያሰሙት።

ይዋል ይደር እንጂ ማንኛውም በግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ቁጭ ብለው ስምምነት ማድረጋቸው እና ወደ ሰላም መምጣታቸው የምይቀር ነው ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።

“ግባችን የጦርነት እሽክርክሪት መፍተል ሳይኾን በተቃራኒው እንዲቋጭ ማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ ያላሰለሰ ጥረት እናደርጋለን”

ሩሲያ ለሰላማዊ ንግግር ከበፊቱም ደጄ አልተዘጋም ባይ ናት። ዩክሬንን ጨምሮ አይዞሽ አለንልሽ ባይ ሀገራት ግን የሰላም ስምምነት እንዳይደረግ እንቅፋት ኾነዋል ስትል ሩሲያ ትከሳለች።

ዩክሬን በበኩሏ የሰላም ውይይት ማድረሁን አልጠላሁትም ነገር ግን ሉዐላዊ ግዛቶቼ በሩሲያ ኀይሎች ተይዘውብኝ እንዴት ነው ሰለሰላም የማወራው የሚል አቋም አላት። ነገር ግን ይህ ጉዳይ የሚስተካከል ከኾነ መነጋግር እንችላለን ስትል ነበር።

አሜሪካ በተመሳሳይ የሩሲያ ጥያቄ ከልብ የመነጨ አይደለም እንዲሁ ለይስሙላ የምትናገረው ነው ስትል ወቅሳለች የነጩ ቤተመንግሥት ቃል አቀባይ የኾኑት ጆን ከርቢ ፕሬዝዳንት ፑቲን ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ምንም ዓይነት ፍላጎት የላቸውም ሲሉ ከሠዋል።

ሩሲያ እና ዩክሬን ዳር ዳር እያሉት ያለው ጦርነቱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፋት ዕውን ይኾናል ወይስ ጦርነቱን አጠናክረው ይቀጥሉታል የሚለውን የምናየው ይኾናል።

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ምታደርገው ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበች። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሌድሚር ዘለንስኪ ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን ተከትሎ ነው ፕሬዝዳንት ፑቲን የዲፕሎማሲያዊ መንገድ ችግራችንን እንፍታ የሚል ጥሪ ያቀረቡት።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-23