ሀገሬ ቲቪ

የቱሪዝም ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመን

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የዐለማችንን ብሎም የሀገራችንን ኢኮኖሚ በእጅጉ ፈትኖታል ።

የዚህ በሽታ መከሰት በስራቸው ላይ ከባድ ጫና ካሳደረባቸው የሀገራችን ድርጅቶች ውስጥም የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቱሪዝም ዘርፉ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ በሽታ መከሰት በኋላ ያሉትን የህዝብ ማጓጓዣ አውሮፕላኖች ወደ ዕቃ ማጓጓዣ ( ካርጎ) በመቀየር ድርጅቱ ላይ የተፈጠፈሩትን ጫናዎች በእጅጉ መቀነሱ ይታወሳል ።

በበሽታው መምጣት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የገባው የቱሪዝም ዘርፉ ግን ካጋጠመው ፈተና በቀላሉ መላቀቅ አዳጋች ሆኖበታል ።

ሆኖም ዘርፉን ዳግም ለማነቃቃት እንዲሁሞ የ ሀገሪቱን መስህቦች ለዓለም ለማሳወቅ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም አስፈላጊ ነውና መስሪያ ቤቱ የግብይት ስርዐቱን የሚያቀላጥፍ ስማርት ካርድ ፣ መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርግ መተግበሪያ እንዲሁም የቱሪዝም ቁጠባ ስርዐት መዘርጋቱን የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ናሲሴ ጫሊ አስታውቀዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር ይፉ ያደረጋቸው ጉዞ የቁጠባ ሒሳብ ፣ ቱሪስት ካርድ እና ቱሪስት መተግበሪያዎች ለጎብኚዎች ምቹ ሁኔታን ከመፍጠራቸው ባሻገር የውጪ ምንዛሬን በማምጣት በኩል ቀላል የማይባል ሚና እንደሚጫወቱ ተነገሯል።

የቱሪዝም ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመን በኮቪድና በሀገራችን በተከሰቱ ግጭቶች ተዳክሞ የነበረውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በመታደግ በኩል የራሱን ሚና እንደሚጫወት የተነገረ ሲሆን ሕብረተሰቡ ዛሬ ይፉ በሆኑት መተግበሪያዎች በመጠቀም ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-12-23