ሀገሬ ቲቪ

ፓስፖርት አሰጣጡ በደላሎች እጅ ወድቋል ተብሏል

የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ለህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ ህግ፣ ለፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ 5 ወር የሰራ ሪፖርቱን አቅርቧል ።

ተቋሙ በ5 ወራት የሰራ አፈጻጸሙ ከ420 ሺ በላይ የፓስፖርት አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ማቅረብ የቻለ ሲሆን ለ141 ሺ ዜጎች ድግሞ የቪዛ አገልገሎትን ሰጥቻለሁ በሏል ።ተቋሙ አግልግሎቱን ለማዘመንም እየሰራ ስለመሆኑ በሪፖርቱ ገልጿል።

ተቋሙ አገልገሎት በሚሰጥባቸው መስሪያ ቤቶች በመገኘት ምልከታ ያደርገው ቋሚ ኮሚቴው አሁንም በፓስፖርት አስጣጥ አገለግሎት ላይ አሁንም መሻሻሎች አለመታየቱን እና የፓስፖርት አስጣጡ በደላሎች እጅ የወደቀ መሆኑ መመልከታቸውን ተናግረዋል ።

ቋሚ ኮሚቴው በሰጠው ግብረ መልስ እና መልከታ ላይ መላሽ የሰጡት የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልገሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ገንበቶ በአገልገሎቱ ወስጥ ደላሎችን የፈጠረው ህዝቡ ነው ተናግረዋል።

በወንድምአገኝ አበበ
2022-12-23