ሀገሬ ቲቪ

የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን መቀሌ ገባ

በአፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን መቀሌ ገባ።

የልዑካን ቡድኑ ወደ መቀሌ ያቀናበት ምክንያት የሰላም ስምምነቱን አተገባበር ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ እንደኾነ ተገልጿል።

በልዑካን ቡድኑ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትም ተካትተዋል።

የልዑካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቐለ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ሲሆን ስምምነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ ነው ተብሏል።

ቡድኑ መቀሌ ሲደርስ በትግራይ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ኀላፊዎች እና የሃይማኖት መሪዎች አቀባበል ተደርጎለታል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-26