የሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ የለስላሳ መጠጦችን ማምረት ማቆሙ ተገለጸ እንደ ሰበን አፕ፣ ሚሪንዳ ፔፕሲ፣ ኩል የተፈጥሮ ማዕድን ውሃ ያሉ መጠጦችን የሚያመርተው እና የዕውቁ ባለሀብት የሼህ ሞሐመድ አል አሙዲን ከሆነው ሜድሮክ የሚመደበው ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ በጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር ምክንያት ሥራውን አቁሟል። የውጪ ምንዛሬ ዕጥረት ፋብሪካው ጥሬ እቃዎችን ከውጪ ለማስገባት እክል እንደፈጠረበት ነው የተሰማው። ካፒታል ጋዜጣ አገኘሁት እንዳለው መረጃ ሞሃ የሚያመርታቸውን የለስላሳ መጠጥ ምርቶች አቁሟል። ሞሃ የለስላሳ መጠጥ መጠጥ ፋብሪካ በጥሬ እቃ እጥረት ምክን ያት ከጥቂት ወራት ጅምሮ ሥራውን በሳምን ሶስት ቀን ብቻ አድርጎ ነበር። ከሁለት ሳምንት በፊት ግን ካጋጠመች ከባድ ችግር አንጻር ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ሥራ ማቆሙ ተሰምቷል ችግሩ እልባት እስኪያገኝ ድረስም ሰራተኞች ከክፍያ ጋር በግዴታ እረፍት እንዲወጡ ተደርገዋል
በሀገሬ ቲቪ
2022-05-03
