ሀገሬ ቲቪ

የዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ጨምሯል ተባለ

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር መጨመሩን ድንበር ተሻጋሪ የሀኪሞች ቡድን አስታወቀ።

በያዝነው ዓመት አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር 22 ሚሊዮን ተሻግሯል ብሏል ቡድኑ።

በአፋር፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ውስጥ ተረጂዎችን ለመድረስ ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችን እየተጠቀመ እንደሚገኝም ይኸው ድንበር ተሻጋሪ የሀኪሞች ቡድን ጠቁሟል።

ከግጭቶች እና አየር ንብረት ለውጥ ባሻገር በሱማሌ ክልል የኮሌራ ወረርሽኝ መቀስቀሱንም በሪፖርቱ ጠቁሟል። በክልሉ ሊበን ዞን ባለው የስደተኞች ጣቢያ ውስጥ ካሉ 72 ሺሕ ሰዎች መካከል በርካቶች በወረርሽኙ መያዛቸውን ቡድኑ አስታውቋል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-12-26