ሀገሬ ቲቪ

በሱዳን ዳርፉር አዲስ ግጭት ተከሰተ

በሱዳን ዳርፉር ግዛት የአረብ ዝርያ ባላቸው እና በሌላቸው ጎሳዎች መካከል በተከሰተ ግጭት ሳቢያ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል።

እስካሁን ከ10 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲኾን ከ20 በላይ የሚኾኑ ደግሞ መሞታቸውን ፕረስ ቲቭ ዘግቧል። በዳርፉር ግዛት በተደጋጋሚ ጎሳን መሠረት ያደረገ ግጭት ይከሰታል።

በዚህ ዓመት ብቻ በተመሳሳይ ግጭት ከዘጠኝ መቶ በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲኾን ከ ሦስት መቶ ሺ በላይ የሚኾኑት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ሪፖርት ያመላክታል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-12-26