ሩስያ ለአውሮፓ በአማራጭ መስመር ነዳጅ ለማቅረብ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።
የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ ሩስያ ለአውሮፓ በያማል ኢሮፕ የነዳጅ መስመር በኩል የተፈጥሮ ጋዟን ለማቅረብ ዝግጇ መሆኗን ገልጸዋል።
ኖቫክ በ11 ወራት ውስጥ ለአውሮፓ 19.4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝን አቅርበናል ፤ በዓመቱ ማብቂያ ወደ 21 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ይደርሳል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል። ሩስያ ለአውሮፓ የምታቀርበውን የተፈጥሮ ጋዝ በተወሰነ መንገድ ብትቀንስም፣ የአህጉሩ ገበያ አሁንም የሩስያን የጋዝ አቅርቦት ይፈልጋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-12-26
